Coffee ShopFebruary 3, 20240 284 በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ስር የሚሰሩ የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ (ጥር 25/2016 ዓ ም፡ ኢ/ቡ/ሻ/ባ)፡ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ስር የሚሰሩ የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት ስልጠና በቢሾፍቱ ፒራሚድ ሆቴል በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡መድረኩን በይፋ የከፈቱት በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡ ናቸው፡፡ አቶ ሰፊሳ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት በባለስልጣን መ/ቤቱ በጀት ብቻ ስራዎችን ማከናወን አስቸጋሪ በመሆኑ በአጋርነት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መጠቀም የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም የዛሬው መድረክ ማተኮር ያለበት የፕሮጀክት ስራዎችን አፈፃፀም መገምገምና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መለየት ዋነኛው ጉዳይ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም የስልጠና እና የግምገማ መድረኩን በአግባቡ ተከታትሎ ለቀጣይ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ግብዓት ሊገኝ እንደሚችል ገልፀዋል፡፡በዚህ መድረክ የክልል ኃላፊዎች፣ የምርምር ማዕከላት፣ የባለስልጣን መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዴስክና የቡድን መሪ ባለሙያዎች እና ሌሎች አጋር አካላት የተገኙ ሲሆን የEU-CAFE፣ የEU YAHU DESIRA ፕሮጀክት፣ የFSRP ፕሮጀክት፣ የ ፕሮጀክት እና የ Spanish cooperation Desira እንዲሁም GI ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ሪፖርቶች በተከታታይ በአስተባባሪዎቹ አማካኝነት በዝርዝር የቀረበ መሆኑን የባለስልጣን መ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳየች ቡድን በቦታው በመገኘት ዘግቧል፡፡ Share